• የወይራ ዘይት መድኃኒት ነው

ባደጉት ሀገራት የወይራ ዘይት ቅርንጫፍ የደስታ፣ የህይወት፣ የብልፅግና እና የለጋሽነት ምልክት ብቻ አይደለም፡፡

አንዳንድ ሠዎች የወይራ ዘይት ቤታቸውን ከአጋንንት፣ ከምቀኝነት እና ከመንፈስ ይጠብቃል ይላሉ፤ ይህን በውይይት መልክ ማቅረብ ከባድ ቢሆንም ስለወይራ ዘይት አስፈላጊነት፣ የጤና ስብስብ እና የውበት ማፍለቂያ ስለመሆኑ ግን ምንም ጥርጥር የለውም፤ ለምሳሌነትም ብዙ ሳሙናዎች ሎሽኖች እና የመዋቢያ ክሬሞች ሲሰሩ አይተናል፡፡

ለብዙ አመታት በሜዲትራኒያን እና በራሽያ አነስተኛ ስፍራ የሚኖሩ የወይራ ዘይትን ጥቅም ሆነ አሰፈላጊነት በደንብ ያውቁታል፤ ሁልጊዜም በኩሽናቸው እና በጠረጴዛቻው ላይ አይጠፋም፤ መቅደሳቸውንም ለማብራት ይጠቀሙበታል፤ ለአምላካቸው ይሰዋሉ፤ ለሽቶነት እና ቆዳቸውን ለማስዋቢያነት ይጠቀማሉ፤ በተለይ ስፖርተኞች በውድድር ወቅት ጡንቻቸውን ለማዳበር ይታሹበታል፣ ይታጠቡበታል ይህም ሰውነታቸው ጉልበት እንዳያጣ ያግዛቸዋል፡፡

በሜዲትራኒያን የሚኖሩ ሠዎች እና ጎረቤቶቻቸው የወይራ ዘይትን ለጤና የሚሰጠውን ጥቅም ሁልጊዜ ይናገራሉ፤ ብዙዎች እንዲጠቀሙም ያበረታታሉ፤ የጤና ባለሞያዎችም ይህንን በሚገባ ይደግፋሉ፤ በተጨማሪም የወይራ ዘይት ያለው በሽታን ለማዳን የሚያግዝ መድኃኒት አዘጋጅተዋል፤ እስከ አሁን ድረስም በቱርክ ኖስትረም የተባለ ከወይራ ዘይት የተሰራ ፈዋሽ መድኃኒት ይገኛል፡፡