• የወይራ ዘይት የልብ ጓደኛ ነው

ዘመናዊ ህክምናዎች የሠው ልጅ በምግብ ውስጥ የወይራ ዘይትን ቢጠቀም ምን ያህል ጤናማ እንደሚሆን ይሰብካሉ፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ እንደ ጭማቂ እንዲጠጣም ያዛሉ፡፡ ለዛም ነው በአሁን ጊዜ በሜዲትራኒያን የሚኖሩ ሠዎች በብዛት አትክልት እና ፍራፍሬን የሚመገቡት ይህም ስጋን ከመመገብ በተሻለ መልኩ ጤናን የመጠበቅ ኃይል አለው፡፡

በወይራ ዘይት ላይ የተሰሩ ብዙ ጥናቶች ስለሚሰጠው ጥቅም አረጋግጠዋል፤ ለዛም ነው ለጤናማ እና ለተስተካከለ ህይወት የወይራ ዘይት ተመራጭ የሚሆነው፤ የልብ ህመም እንዳይከሰትም ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፤ በአለም ላይ በተደረገው ጥናት እና ምርምር በ2000ዓ.ም ለንደን ውስጥ በተደረገው ትልቅ ስብሰባ የወይራ ዘይት ለልብ ጤንነት አሰፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በሠው ልጅ ለሚሰጠው ዋጋም ወርቃማ ፈሳሽ የሚል ስያሜ ተሰቶታል፡፡

ልክ እንደ ሁሉም የአትክልት ዘይቶች የወይራa ዘይትም ተስማሚ እና ጤናማ ስብን እንደሚለግስ ይታወቃል ምክንያቱም የእንስሳቶች ስብ በደም ውስጥ የኮልስትሮል መጠንን እንደሚጨምር ይታወቃል፤ የአትክልት ዘይት ደግሞ ከእፅዋቶች ፍሬ የሚገኝ ስብን ይዟል ይህ ደግሞ ጤናማ እና ተመራጭ አድርጎታል፡፡

በተጨማሪም የወይራ ዘይት ከሁሉም የአትክልት ዘይቶች በሚበልጥ ሁኔታ ከስብ ነፃ እንደሆነ ባለሞያዎች አረጋግጠዋል፡፡ ንፁህ የወይራ ዘይት ልክ እንደ ፍርፍሬ ጭማቂ እንደተጨመቀ መጠጣት ይችላል፤ ነገርግን ከወይራ ዘይት በቀር ማንኛውም የአትክልት ዘይት መጠጣት አይቻልም፡፡

ንፁህ የወይራ ዘይት የሚገኘው በሂደት ሲሆን ከሌሎች የአትክልት ዘይቶች በበለጠ በውስጡ ፖሊአንሳቹሬትድ ፋቲ አሲድ ይዟል፤ በተጨማሪም 70 በመቶ የሚሆን ሞኖአንሳቹሬትድ ፋቲ አሲድ ይገኝበታል፤ በሜዲትራኒያን የሚገኙ ሀገሮች የወይራ ዘይትን በመጠጣት ይጠቀሙታል፤ ይህ ተዓምረኛው ፈሳሽ ጥሩ የስብ መጠን እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም በሊፖፕሮቲን አማካኝነት ኮልስትሮልን በመቀነስ የሰውነትን መጠንከር እና የደም ግፊትን ያስተካክላል፡፡