• የወይራ ዘይት ስብን ይከላከላል

ኮልስትሮል(ስብ) ከመጠን ካላለፈ ለሠው ልጅ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ለህዋሶቻችን ጠቃሚ ስለሆነ፡፡

ኮልስትሮል(ስብ) በጉበት ውስጥ በመመረት በሰውነታችን ውስጥ ይሰራጫል፤ በህዋሶቻችን ውስጥ ጠቃሚ የሆነውን ስብ የሚሸከመው ሊፖፕሮቲን በዝቅተኛ እና በከፍተኛ መጠን ይከፋፈላል፤ ይህም የደም ስርን ከማጥበብ በላይ ሊደፍን ይችላል፤ በዚህ ጊዜ በከፍተኛ መጠን የሚከፋፈለው ተግባር የደም ስርን በማመቻቸት ከበቂ በላይ የሆነውን አላስፈላጊ ስብ ያጣራል፡፡ በዚህ መልኩ በሰውነታችሁ ውስጥ ያለውን አላስፈላጊ የስብ መጠን ለማስወገድ ቀላል ይሆናል፡፡

ቅባት ያላቸው ስቦች በደም ስር ውስጥ የኮልስትሮል መጠንን ይጨምራሉ ግን የአትክልት ዘይት በፖሊ ሳቹሬትድ አሲድ የበለፀገ ስለሆነ ይህ እንዳይከሰት ወይም እንዲቀንስ ያደርጋል፤ ነገር ግን በወይራ ዘይት ውስጥ የሚገኘው ኦሊክ አሲድ በሞኖአንሳቹሬትድ ሲድ የበለፀገ ነው፤ ይህም ጎጂ የሆነውን ስብ ይከላከላል፤ በሌላ አባባል በደም ውስጥ የሚገኘውን አላስፈላጊ ስብ በቀላሉ በማስወገድ ጠቃሚውን ስብ ይጨምራል፡፡