• ወጣት ሆኖ የመቆየት ሚስጥር

የወይራ ዘይት ወጣት ያደርገናል፤ የወይራ ዘይት እውነተኛ ተፈጥሮዓዊ ምግብ ነው፤ ላይኖሊክ አሲድ የተባለ የጡት ወተትን የሚተካ ንጥረነገር ስላለው ህፃናትን ጡት ለማስጣል መፍትሄ ይሆናል፡፡

በተለይ ጡት ለማጥባት ለሚቸገሩ እናቶች ቅባት በሌለው በላም ወተት ውስጥ ትንሽ የወይራ ዘይት ጠብ አድርገው መጠቀም ይችላሉ፡፡ የወይራ ዘይት የተመገብነውን ምግብ ለመፍጨት ቀላል ከመሆኑ በተጨማሪ ለየትኛውም እድሜ ተስማሚ የሆነ ቫይታሚንን እና ሚንራሎችን ይዟል፡፡ ክሎሮፊልም የተባለ ጠቃሚ ንጥረነገርም በወይራ ዘይት ውስጥ ይገኛል፤ ይህ ንጥረነገር ለወይራ ዘይት የሚሰጠው ቀለም ብቻ ሳይሆን ህዋሳት እንዲያድጉ እና ቁስል በአፋጣኝ እንዲድን ያደርጋል፡፡

የወይራ ዘይት ጥቅሞች ውስን አይደሉም፤ እንደሚታወቀው በአሲድ ውስጥ ያለው ቫይታሚን ኢ እና ኬ በተጨማሪም የፀረ-ብግነት ባህሪያት የህፃናትን አጥንት በማጠንከር ከፍተኛ ሚናን ያጫወታሉ፤ እንዲሁም በጎልማሳ ሴቶች ላይ በብዛት የሚከሰተውን የአጥንት ብግነት ያስቆማል፤ ህብረህዋስን እና አባልአካልን በማደስ እርጅናን ሲያዘገይ፤ አዕምሮን ለማበልፀግ እና ወሲባዊ እንቅስቃሴን ለማዳበር ያግዛል፤ በተጨማሪም የሆድ ድርቀትን ጨምሮ ለተለያዩ ህመም እና ቁስሎች መድኃኒት ነው፡፡