• ያጋሩ
  • ክሪታን ከባብ
ውህዶች

ውህዶች 6 ያህል የተላጡ artichokes (በለጋነቱ) የሚበላ ተክል)

600 ግራም የበግ ስጋ፣ በኪዩብ ቅርጽ የተከተፈ

1 የሻይ ብርጭቆ የኢኪዝ የሱፍ ዘይት

20-25 አናት ባሮ ሽንኩት

1 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት

አንድ እፍኝ ኩከምበር

አንድ ስኒ አደንጓሬ ፣ አስፈላጊ ከሆነ

አዘጋጃጀት

ባሮ ሽንኩት እና ነጭ ሽንኩርቱን ይላጡ እና የኢኪዝ ሱፍ ዘይት በመጨመር አንድ ላይ ያብስሉ፡፡ ይህንን ባሮ ሽንኩርትይ እና ነጭ ሽንኩት በመካከለኛ ሙቀት ለ5 ደቂቃ ያህል ያብስሉ እና ወደ ገበታ ሳህኑ ይገልብጡ፡፡ የተከተፈውን ስጋ መረቅ እስከሚወጣው ድረስ ያብስሉ፡፡ ስጋው ሙክክ ብሎ እስከሚበስል ድረስ በፈላ ውሃ ይቀቅሉ፡፡ በለጋነቱ የሚበላውን (artichokes) በትናንሹ በመቁረጥ በባሮ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት ጋር አብሮ ወደበሰለው ስጋ በመክተት ትንሽ ጨው እና ሚጥሚጣ ይጨምሩ፡፡ እርስዎ ከፈለጉ የተወሰነ አደንጓሬ በመጨመር በመካከለኛ ሙቀት ያብስሉ፡፡ በለጋነቱ የሚበላው ተክል ሙሉ በሙሉ እስከሚበስል ድረስ የድስቱን ክዳን በአግባቡ ይዝጉት፡፡ የምግብ ማብሰያ ድስቱን ምድጃው ላይ ካነሱ በኋላ ጥቂት ኩከንበር ይጨምሮ እና ለበላተኛው በትኩስነቱ ያቅርቡ፡፡ የተባረከ ገበታ ይሁንልዎ!