• ያጋሩ
  • ከአትክልት ምግብ ጋር የሚቀርብ የሽንጥ ስጋ ጥብስ
ውህዶች

400 ግራም የሽንጥ ስጋ/ስቴክ

2 ፍሬ ድንች

2 ፍሬ ካሮት

2 ፍሬ የቲማቲም ድልህ

እንጉዳይ

4 ፍሬ ቲማቲም

ፍሬሽ ጦሲኝ

አዝመሪኖ

የኢኪዝ የገበታ ዘይት

ጨው

ቁንዶ በርበሬ

ከምግቡ በላይ - አንድ ክዳን ሳህን እርጎ

አዘጋጃጀት

ድንቾቹን እና ካሮቶቹን ይላጡ እና ይክተፉ፡፡ እንጉዳዮቹን በቀጫጭኑ በመክፈት ይዳምጡ፣ እንዲሁም በምግብ መጥበሻ ትሪው ላይ ይጨምሩ፡፡ ከዚያም ጨው፣ ሚጥሚጣ/በርበሬ እና የወይራ ዘይት ይጨምሩ፡፡ በአትክልት ምግቡ ላይ ትንሽ ጦሲኝ ይጨምሩ እና በአንድ ላይ ይቀላቅሉት፡፡ ከዚያም ውሁዱን 200 ዲግሪ ሙቀት ባለው ኦቨን/ምድጃ ላይ ያብስሉ፡፡ የሽንጥ ስጋውን በጣትዎ ውፍረት ልክ በቀጫጭኑ ይቁረጡ፡፡ ከዚያም በክዳን ሳህኑ ውስጥ በመጨመር በፍሬሽ አዝመሪኖ እና የኢኪዝ የገበታ ዘይት ይለውሱት፡፡ ስቴኩን በጋለው መጥበሻ ላይ በመጨመር ያብስሉ፡፡ ባናቱ ላይም ጨው እና ሚጥሚጣ/በርበሬ ይጨምሩ፡፡ የተላጡትን ቲማቲሞች በረጃጅሙ በጉረድ ወደ መጥበሻው ይጨምሩ እና በኢኩዝ የገበታ ዘይት ያብስሉ፡፡ የተጠበሰውን ቲማቲም በእርጎው አናት ላይ ይጨምሩ እና ጥብሱን/ስቱኩን በቲማቲሙ ላይ ያፍስሱት፡፡