• ያጋሩ
  • ኦርዞ ፒላፍ ከካሮት ጋር
ውህዶች

ውህድ

2ኩባያ ኦርዞ

1የሻሂ ብርጭቆ የጣሳ የታሸገ ቦቆሎ

1ፍሬ ሽንኩርት

2ራስ ነጭ ሽንኩርት

2ፍሬ ካሮት

የተፈጨ የምግብ ማጣፈጫ ቅጠል (ፓርሲሊ)

3የሻሂ ማንኪያ የኤኪዝ ወይራ ዘይት

3ኩባያ የፈላ ውሃ

1የሻሂ ማንኪያ ቀረፋ

1የቡና ማንኪያ የተፈጨ ስኳር እና ጨው

አዘጋጃጀት

ቀይ ሽንኩርት እና ነጭ ሽንኩርት ይላጡ እና ይፍጩ፡፡ የኤኪዝ ወይራ ዘይቱን በጋለው መጥበሻ ላይ በማቅለጥ፣ የተፈጨውን ሽንኩርት እና ነጭ ሽንኩርት በአንድ ላይ በመጨመር ያቁላሉ፡፡ ካሮቶቹን ይጨምሩ እና ለጥቂት ደቂቃዎች ያብስሉ፡፡ ከዚያም ካሮቱን በሽቦ ማጥለያ ዘይቱን ያንጠፍጥፉ፡፡ በፈላው ውሃ ውስጥ ኦርዞውን ይጨምሩ እና ያማስሉ፡፡ ውሃው ሙሉ በሙሉ እስከሚመጠጥ ጊዜ ድረስ ኦርዞውን በዝቅተኛ ሙቀት ያብስሉ፡፡ መጥበሻውን ከምድጃቸው ላይ ካነሱት በኋላ ፒላፉን በኤኬዝ የወይራ ዘይት ይለውሱ፡፡ የበሰለውን ካሮት በማቀላቀል ጥቂት በጣሳ ከታሸገው ቦቆሎ ይጨምሩ፡፡ ምግቡን በትኩስነቱ ያቅርቡ፡፡ የተባረከ ገበታ ይሁንልዎ!